Skip to main content

Language Services - አማርኛ (Amharic)

የተተረጎሙ ምንጮች

የኢንተርኔት አሳሽ ትርጉም

የሚችጋን ስቴት መምሪያ (Michigan Department of State) በሦስተኛ አካል መተግበሪያ ወይም ኢንተርኔት አሳሽ በኩል የተሠራውን ማንኛውንም ትርጎሞችን በመጠቀም ለሚከሰተው ማንኛውም ወይም ሙሉ በሙሉ ክስረት ኃላፊነት እና ቅሬታን የማይቀበል መሆኑን ይገልጻል። የሦስተኛ አካል አገልግሎትን መጠቀም በተጠቃሚው በራሱ ኃላፊነት ይሆናል። የሦስተኛ ወገን አገልግልቶችን የሚመለከት መረጃ አመቺ የሚሆን ከሆነ ብቻ ይሰጣል።

ሳፋሪ በዓረብኛ፣ በቻይንኛ (ቀለል ባለው)፣ በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛ፣ በጣሊያኒኛ፣ በጃፓንኛ፣ በኮሪያንኛ፣ በፖርቹጋልኛ፣ በሩሽኛ፣ እና በስፓንኛ የኢንተርነት ትርጉም ይሰጣል።

ዴስክቶፕ

  1. የሳፋሪ የኢንተርነት መክፈቻን ይክፈቱ እና ቪው View ይምረጡ፤ ከዚያም ከላይ ወደታች ከሚለው መዘርዝር ውስጥ መርጠው ይተርጉሙ።
  2. የእርስዎን አሳሽ በሚመርጡት እና ከእንግሊዝኛ ውጪ የሆነ ቋንቋ ይሙሉ።
  3. መተርጎም ወደሚፈልጉት ድረገጽ ይሂዱ።
  4. የሚተረጉመው ቁልፍ ይታያል። ለሁሉም ገጾች ትርጉሞች ላይገኙ ይችላሉ።
  5. የሚተረጉመውን ቁልፍ እና የቋንቋ ምርጫዎን ይምረጡ

አይፎን ወይም አይፓድ

  1. የሳፋሪ ኢንተርኔት መክፈቻን በሞባይል ስልክዎ ላይ ይክፈቱ እና መተርጎም ወደሚፈልጉበት ገጽ ላይ ይሂዱ።
  2. የዌብሳይት አማራጮችን ለማየት ከአድራሻው ማሳያ ቀጥሎ ያለውን “aA” የሚለውን አይከን ይምረጡ። ከተቆልቋይ ምናሌ ውስጥ Translate to የሚለውን ይምረጡ እና ይፈለጉትን ቋንቋ ይምረጡ፡፡
  3. ብቅ ባይ ምናሌ የሚታይ ከሆነ Enable Translationን ይምረጡ። ትርጉምን እንዲሠራ ለማድረግ አንዴ ብቻ የሚጠየቁ እንደሆነ ያስታውሱ።
  4. ከIOS 14.0 የቀደመ ኦፕሬቲንግ ስርዓት ያላቸው የአፕል (Apple) መሳሪያዎች ይህንን መለያ ባህሪን አያካትቱም። ትርጉሞችን ለማግኘት የጉግል ትርጉም (Google Translate) መተግበሪያን ወይም ማይክሮሶፍት ተርጓሚ (Microsoft Translator) መተግበሪያን ወደ የእርስዎ መሳሪያ ያውርዱ

ዴስክቶፕ

  1. የክሮም (Chrome) አሳሽን ይክፈቱ እና ለመተርጎም ወደሚፈልጉት ድረ–ገጽ ይሂዱ። ብቅ ባይ የጉግል ትርጉም (Google Translation) ሜኑ ሊመጣ ይችላል።
  2. ገጹን ለመተርጎም ከምናሌው ላይ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  3. የትርጉም ምናሌው ካልመጣ፣ የጎግል ትርጉም (Google Translate) ቁልፍን ይምረጡ። ገጹን ለመተርጎም ከምናሌው ላይ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  4. ተጨማሪ የቋንቋዎችን ትርጉም ለመድረስ፣ የጉግል ትርጉም (Google Translate) ቁልፍን ይምረጡ እና የተግባር ምናሌ ምልክትን ይምረጡ።
  5. ከተቆልቋይ ምናሌ ውስጥ፣ Choose Another Language የሚለውን ይምረጡ እና ከተቆልቋይ ምናሌ ውስጥ የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።

አንድሮይድ ስልክ ወይም ታብሌት

  1. በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ የክሮም (Chrome) አሳሽን ይክፈቱ እና ለመተርጎም ወደሚፈልጉት ድረ–ገጽ ይሂዱ።
  2. የጎግል ትርጉም (Google Translation) ምናሌ ሊመጣ ይችላል።
  3. ገጹን ለመተርጎም ከምናሌው ላይ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  4. ተጨማሪ ቋንቋዎችን ለትርጉም ለማግኘት፣ የእርምጃ ምናሌ ምልክትን ይምረጡ እና More Languages የሚለውን ይምረጡ፣ ከዚያም ከተቆልቋይ ምናሌው ውስጥ የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  1. የMicrosoft Edge አሳሽን ሲከፍቱ በአሳሽዎ የላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦችን ይምረጡ እና ከዚያ ከተቆልቋዩ ዝርዝር ውስጥ Settingsን ይምረጡ።
  2. ከአሳሽዎ መስኮት በስተግራ በኩል ያለውን፣ Languages የሚለውን ይምረጡ ከዚያም Add languagesየሚለውን በመምረጥ እና መጠይቆቹን በመከተል የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  3. በእርስዎ ምርጫ በሆነው ቋንቋ ያልተተረጎመ ገጽ ከጎበኙ፣ በአድራሻ አሞሌው ላይ ብቅ ባይ የትርጉም ምናሌ ሊታይ ይችላል።
  4. የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ለመምረጥ መጠይቆቹን ይከተሉ እና ገጹን ለመተርጎም Translate የሚለውን ይምረጡ።