Skip to main content

የቋንቋ አገልግሎት - አማርኛ (Amharic)

የተተረጎሙ ምንጮች

የኢንተርኔት አሳሽ ትርጉም (መደቡን መምረጥ)

የሚችጋን ስቴት መምሪያ (Michigan Department of State) በሦስተኛ አካል መተግበሪያ ወይም ኢንተርኔት አሳሽ በኩል የተሠራውን ማንኛውንም ትርጎሞችን በመጠቀም ለሚከሰተው ማንኛውም ወይም ሙሉ በሙሉ ክስረት ኃላፊነት እና ቅሬታን የማይቀበል መሆኑን ይገልጻል። የሦስተኛ አካል አገልግሎትን መጠቀም በተጠቃሚው በራሱ ኃላፊነት ይሆናል። የሦስተኛ ወገን አገልግልቶችን የሚመለከት መረጃ አመቺ የሚሆን ከሆነ ብቻ ይሰጣል።

ሳፋሪ በዓረብኛ፣ በቻይንኛ (ቀለል ባለው)፣ በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛ፣ በጣሊያኒኛ፣ በጃፓንኛ፣ በኮሪያንኛ፣ በፖርቹጋልኛ፣ በሩሽኛ፣ እና በስፓንኛ የኢንተርነት ትርጉም ይሰጣል።

ዴስክቶፕ

  1. የሳፋሪ የኢንተርነት መክፈቻን ይክፈቱ እና ቪው View ይምረጡ፤ ከዚያም ከላይ ወደታች ከሚለው መዘርዝር ውስጥ መርጠው ይተርጉሙ።
  2. የእርስዎን አሳሽ በሚመርጡት እና ከእንግሊዝኛ ውጪ የሆነ ቋንቋ ይሙሉ።
  3. መተርጎም ወደሚፈልጉት ድረገጽ ይሂዱ።
  4. የሚተረጉመው ቁልፍ ይታያል። ለሁሉም ገጾች ትርጉሞች ላይገኙ ይችላሉ።
  5. የሚተረጉመውን ቁልፍ እና የቋንቋ ምርጫዎን ይምረጡ

አይፎን ወይም አይፓድ

  1. የሳፋሪ ኢንተርኔት መክፈቻን በሞባይል ስልክዎ ላይ ይክፈቱ እና መተርጎም ወደሚፈልጉበት ገጽ ላይ ይሂዱ።
  2. የዌብሳይት አማራጮችን ለማየት ከአድራሻው ማሳያ ቀጥሎ ያለውን “aA” የሚለውን አይከን ይምረጡ። ከተቆልቋይ ምናሌ ውስጥ Translate to የሚለውን ይምረጡ እና ይፈለጉትን ቋንቋ ይምረጡ፡፡
  3. ብቅ ባይ ምናሌ የሚታይ ከሆነ Enable Translationን ይምረጡ። ትርጉምን እንዲሠራ ለማድረግ አንዴ ብቻ የሚጠየቁ እንደሆነ ያስታውሱ።
  4. ከIOS 14.0 የቀደመ ኦፕሬቲንግ ስርዓት ያላቸው የአፕል (Apple) መሳሪያዎች ይህንን መለያ ባህሪን አያካትቱም። ትርጉሞችን ለማግኘት የጉግል ትርጉም (Google Translate) መተግበሪያን ወይም ማይክሮሶፍት ተርጓሚ (Microsoft Translator) መተግበሪያን ወደ የእርስዎ መሳሪያ ያውርዱ

ዴስክቶፕ

  1. የክሮም (Chrome) አሳሽን ይክፈቱ እና ለመተርጎም ወደሚፈልጉት ድረ–ገጽ ይሂዱ። ብቅ ባይ የጉግል ትርጉም (Google Translation) ሜኑ ሊመጣ ይችላል።
  2. ገጹን ለመተርጎም ከምናሌው ላይ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  3. የትርጉም ምናሌው ካልመጣ፣ የጎግል ትርጉም (Google Translate) ቁልፍን ይምረጡ። ገጹን ለመተርጎም ከምናሌው ላይ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  4. ተጨማሪ የቋንቋዎችን ትርጉም ለመድረስ፣ የጉግል ትርጉም (Google Translate) ቁልፍን ይምረጡ እና የተግባር ምናሌ ምልክትን ይምረጡ።
  5. ከተቆልቋይ ምናሌ ውስጥ፣ Choose Another Language የሚለውን ይምረጡ እና ከተቆልቋይ ምናሌ ውስጥ የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።

አንድሮይድ ስልክ ወይም ታብሌት

  1. በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ የክሮም (Chrome) አሳሽን ይክፈቱ እና ለመተርጎም ወደሚፈልጉት ድረ–ገጽ ይሂዱ።
  2. የጎግል ትርጉም (Google Translation) ምናሌ ሊመጣ ይችላል።
  3. ገጹን ለመተርጎም ከምናሌው ላይ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  4. ተጨማሪ ቋንቋዎችን ለትርጉም ለማግኘት፣ የእርምጃ ምናሌ ምልክትን ይምረጡ እና More Languages የሚለውን ይምረጡ፣ ከዚያም ከተቆልቋይ ምናሌው ውስጥ የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  1. የMicrosoft Edge አሳሽን ሲከፍቱ በአሳሽዎ የላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦችን ይምረጡ እና ከዚያ ከተቆልቋዩ ዝርዝር ውስጥ Settingsን ይምረጡ።
  2. ከአሳሽዎ መስኮት በስተግራ በኩል ያለውን፣ Languages የሚለውን ይምረጡ ከዚያም Add languagesየሚለውን በመምረጥ እና መጠይቆቹን በመከተል የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  3. በእርስዎ ምርጫ በሆነው ቋንቋ ያልተተረጎመ ገጽ ከጎበኙ፣ በአድራሻ አሞሌው ላይ ብቅ ባይ የትርጉም ምናሌ ሊታይ ይችላል።
  4. የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ለመምረጥ መጠይቆቹን ይከተሉ እና ገጹን ለመተርጎም Translate የሚለውን ይምረጡ።
 

የገንዘብ ዝውውሮች እና አገልግሎቶች የግዛቱ ዋና ጸሐፊ

  • የቅርንጫፍ ጉብኝት ትርጓሜ

    የቅርንጫፍ ቢሮዎች ሙከራ ላልሆኑ አገልግሎቶች በስልክ እና በመሳሪያ የታገዘ ትርጉም ይሰጣሉ። ይህንን አገልግሎት በቀጠሮዎ ጊዜ መጠየቅ ይችላሉ። አስተርጓሚ ለማግኘት ቀደም
    ብሎ ማሳወቅ ወይም መጠየቅ አያስፈልግም። ለእገዛ ወይም ለድጋፍ፣ እባክዎን ወደMDOS-Access@Michigan.gov ኢሜይል ያድርጉ።

     

  • ሁሉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮዎች ለአሽከርካሪ እውቀት መመዘኛ ፈተናዎች የተተረጎሙ ፈተናዎችን በሚከተሉት ቋንቋዎች ያቀርባሉ፦

    • አልባኒያኛ
    • አረብኛ
    • ቻይንኛ
    • ዳሪኛ
    • English
    • ፋርፈረንሳይኛ
    • ግሪክኛ
    • ሂንዲ
    • ጣልያንኛ
    • ጃፓንኛ
    • ኮርያኛ
    • ፓሽቶ
    • ፖላንድኛ
    • ፖርቹጋልኛ
    • ሩስያኛ
    • ስፐይንኛ
    • ዩክሬንኛ
    • ቬትናምኛ
    • ባንግላ
    • በርሚስ
    • ከለዳዊኛ
    • ካረን
    • ኪምቤምቤ
    • ኪንያርዋንዳ
    • ኪሩንዲ
    • ላኦ
    • ማላይ
    • ፑንጃቢ
    • ኡርዱ
    • ሩማንኛ
    • ስዋሕሊ

    የአሽከርካሪው፣ ትንሹ ሞተር ሳይክል፣ ሞተር ሳይክል፣ እና የመዝናኛ (ደብል R) የእውቅና ፈተናዎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮዎች ውስጥ በሚከተለው ቋንቋዎች ይሰጣሉ፦

    • English
    • ስፐይንኛ
    • አረብኛ

    ከዚህ በላይ ላልተዘረዘሩት ቋንቋዎች፣ ስለተፈቀደላቸው አስተርጓሚዎች መረጃ ለማግኘት በ888-SOS-MICH (888-767-6424) በመደወል፣ ወደ MDOS-
    Access@Michigan.gov

    በኢሜል በመላክ ወይም የግዛቱ ዋና ጸሐፊን በመጎብኘት ማግኘት ይችላሉ።

    የተፈቀደላቸው አስተርጓሚዎች በተወሰኑ የግዛቱ ዋና ጸሐፊ ውስጥ አገልግሎት ሊሰጡ ይችላሉ እና ክፍያ እንዲከፍሉ ማድረግ የተከለከለ ነው።

    የአንድ ጊዜ የሙከራ አስተርጓሚ በጎ ፈቃደኞች

    ለፈተና፣ ለፍርድ ቤት ችሎት ወይም ለድጋሚ ፈተና እርስዎን ወክሎ የሆነ ግለሰብ እንዲያስተርጉም ከፈለጉ፣ እንደ የአንድ ጊዜ አስተርጓሚ ሆነው ለማገልገል ማመልከቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የአንድ ጊዜ አስተርጓሚዎ ዕቅድ ከተያዘለት ጉብኝትዎ አስቀድሞ በመምሪያ ክፍሉ ፈቃድ ሊሰጠው ይገባል እንዲሁም ለሙከራዎ፣ ለፍርድ ቤት ችሎትዎ ወይም ለድጋሚ ፈተናዎ ብቻ መተርጎም ይችላል።

    የአንድ ጊዜ አስተርጓሚ ለመሆን ማመልከቻ ለማስገባት፣ አንድ ግለሰብ የሚከተሉትን ማድረግ አለበት፡-

    • የበጎ ፈቃደኞች አስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ማመልከቻ ይሙሉ እና ይፈርሙ። ለአንድ ጊዜ አስተርጓሚ ምርጫውን ይምረጡ
    • ትክክለኛ፣ ጊዜው ያላለፈበት የመንጃ ፍቃድ ወይም መታወቂያ ፎቶ ወይም ቅጂ ማቅረብ አለባቸው

    ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶች በፖስታ፣ በፋክስ ወይም በኢሜይል ወደሚከተለው መላክ አለባቸው፦

    Michigan Department of State
    Enforcement Division
    P.O. Box 30708
    Lansing, MI 48909

    ፋክስ፦ 517-335-3241

    ኢሜይል፦ SOS-OIS@Michigan.gov

    አንድ ጊዜ መምሪያ ክፍሉ ማመልከቻውን ካየው፣ የድርጅቱ ሠራተኛ የአንድ ጊዜ የትርጉም አገልግሎቶችን ለማግኘት እንደተፈቀደላቸው ለማሳወቅ አመልካቹን ሰው ሊያገኙ ይችላሉ።

     

  • የተሽከርካሪ ታርጋ እድሳት፣ የመንጃ ፍቃድ ወይም የመታወቂያ (ID) እድሳት እና የባለቤትነት ጥያቄ ማቅረብን ጨምሮ ብዙ ግብይቶች በመስመር ላይ ሊጠናቀቁ ይችላሉ። በእርስዎ የኢንተርኔት መክፈቻ ላይ ራሱን እንዲተረጉም በሚያደርገው በመጠቀም፣ ዌብሳይታችን ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን እርስዎ በሚመርጡት ቋንቋ በኢንተርኔት ቀጥታ መስመር ላይ ዝውውሩዎቹን ይፈጽሙ። የሚቺጋን ግዛት የመምሪያ ክፍል ድረ–ገጽ እንዴት ራሱን በራሱ እንደሚተረጉም መመሪያዎቹን ለማየት ከዚህ በፊት የነበረው ገጽ ይጎብኙ።

    ወደ ኢንተርኔት ቀጥታ መስመር አገልግሎቶች ይሂዱ

  • የተሽከርካሪ ምዝገባን፣ ቦሎ እና ታርጋን ለማደስ ወይም ፈቃድዎን ወይም መታወቂያዎን ለማደስ፣ አዲስ ፎቶ የማያስፈልግ ከሆነ የራስ አገልግሎት ጣቢያን ይጎብኙ። ሁሉም 160+ የግዛቱ ዋና ጸሐፊ የራስ-አገልግል ጣቢያዎች በሚከተሉት ቋንቋዎች እያስተረጎ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ፦

    • አረብኛ
    • ቤንጋሊ
    • English
    • ፈረንሳይኛ
    • ማንደሪን
    • ፓሽቶ
    • ስፐይንኛ
    • ስዋሕሊ
    • ቬትናምኛ

    በራስ-አገልግል ጣቢያ ላይ ለሚደረግ ለእያንዳንዱ ዕቃ ግብይት የ$4.25 የአገልግሎት ክፍያ ይከፈላል።

    የራስ-አገልግል ጣቢያን ያግኙ

  • አብዛኛዎቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግብይቶች በኦንላይን ወይም በፖስታ ሊጠናቀቁ ይችላሉ። ብዙ የመንጃ ፍቃድ እና የመታወቂያ ግብይቶች እና አብዛኛዎቹ የተሽከርካሪዎች ታርጋ እድሳት ግብይቶች በራስ-አገልግል ጣቢያ ሊደረጉ ይችላሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ቢሮ መሄድ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፣ የቢሮ ጉብኝት ቀጠሮ እንዲያስይዙ በጥብቅ ይበረታታል። ጉብኝቶች ከስድስት ወራት በፊት አስቀድመው ሊታቀዱ ይችላሉ፡፡

    በመረጡት ቋንቋ በመስመር ላይ የጉብኝት ቀጠሮ ለማስያዝ ፣ በራስ-ሰር የመተርጎም ባህሪ ያለው አሳሽ እየተጠቀሙ መሆንዎን ያረጋግጡ። ወይም ወደ 888-SOS-MICH 6424-767-(888) ለቢሮ በመደወል ጉብኝት ቀጠሮ ያስይዙ።


    የቢሮ ጉብኝትን ያስይዙ

ምርጫዎች እና የድምጽ አሰጣጥ መረጃ

  • የሚከተሉት ከሆኑ በሚቺጋን ውስጥ ድምጽ ለመስጠት መመዝገብ ይችላሉ፡-

    • የአሜሪካ ዜጋ
    • እድሜው ቢያንስ 17.5 አመት (በ16 ቅድመ መመዝገብ)
    • በአሁኑ ጊዜ በእስር ቤት ወይም በወህኒ ቤት ውስጥ ቅጣት ላይ ካልሆኑ
    • የሚቺጋን ነዋሪ

    የምዝገባዎን ሁኔታ ያረጋግጡ

    በራስ-ሰር የመተርጎም ባህሪ ያለውን አሳሽ በመጠቀም፣ የእርስዎን የድምጽ መስጫ ምዝገባ ሁኔታን በ Michigan.gov/Vote ላይ ማረጋገጥ ይችላሉ።

    እንዴት መመዝገብ ይቻላል

    ድምጽ ለመስጠት ከምርጫው ቀን እስከ 2 ሳምንታት በፊት ቀደም ብለው በመስመር ላይ (በሚቺጋን የአሽከርካሪ ፍቃድ እና በመታወቂያ ቁጥር) ወይም በፖስታ መመዝገብ ይችላሉ። እንዲሁም በምርጫ ቀን ከ 8 p.m. በፊት ወይም እስከዚያ ድረስ በማንኛውም ሰዓት በአካባቢዎ ፀሐፊ ቢሮ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።

    ድምጽ ለመስጠት በፖስታ ወይም በአከባቢዎ ፀሐፊ ቢሮ ሲመዘገቡ፣ የሚቺጋን የአሽከርካሪ ፍቃድ ወይም መታወቂያ የማያስፈልግዎት ሲሆን በምትኩ የማህበረሰብ ዋስትና ቁጥርዎን የመጨረሻዎቹን አራት አሃዞች መስጠት ይችላሉ።

    እባክዎን ያስታውሱ ምርጫ በተደረገ በ14-ቀናት ውስጥ የነዋሪነት ማረጋገጫዎን ይዘው በአካል በፀሐፊዎ ቢሮ መመዝገብ አለብዎት።

    በኦንላይን ይመዝገቡ፦ በመረጡት ቋንቋ የኦንላይን የመራጮች ምዝገባ በMichigan.gov/Vote ላይ ለማግኘት በራስ-የመተርጎም ባህሪ ያለውን አሳሽ ይጠቀሙ።

    የሚከተለው ከሆነ በኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ፦

    • ተቀባይነት ያለው የሚቺንጋን ግዛት መታወቂያ ወይም የመንጃ ፈቃድ ካልዎት
    • የመጨረሻውን 4 የማኅበራዊ ዋስትና (Social Security) ቁጥርን የሚያውቁ ከሆነ
    • ዕድሜዎ ቢያንስ 17.5 ዓመት ነው (በ16 ቅድመ መመዝገብ)
    • እርስዎ ምርጫው ከመድረሱ በፊት ባሉት በ14 ቀናት ውስጥ አይደሉም

    ምርጫው ከመድረሱ ባሉት በ14 ቀናት ውስጥ ወይም በምርጫው ቀን ላይ በመስመር ላይ ከተመዘገቡ በዚያ ምርጫ ላይ ድምጽ ለመስጠት ብቁ አይሆኑም። መታወቂያዎን ወይም የመንጃ

    ፈቃድዎን ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ አሳድሰው ከሆነ በኢንተርኔት ቀጥታ መስመር ላይ መመዝገብ የተከለከለ ነው።

    በኦንላይን ይመዝገቡ / የአሳሽ ትርጓሜ

    መታተም በሚችሉ የመመዝገቢያ ቅጽን በመጠቀም ይመዝገቡ፦ የተተረጎመውን፣ ሊታተም የሚችለውን የድምጽ መስጫ መመዝገብያ ቅጽን በመጠቀም ድምጽ ለመስጠት መመዝገብ ይችላሉ። እንደሚከተለዉ ከሆነ የታተመ የምዝገባ ቅጽ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡-

    • ትክክለኛ የሚቺጋን ግዛት መታወቂያ ወይም የአሽከርካሪ ፍቃድ ወይም የማህበራዊ ዋስትና ቁጥርዎ የመጨረሻ 4 አሃዞች ካለዎት(አንዱ ብቻ ነው የሚፈለገው)።
    • ዕድሜዎ ቢያንስ 17.5 ዓመት ነው (በ16 ቅድመ መመዝገብ)
    • እርስዎ ምርጫው ከመድረሱ በፊት ባሉት በ14 ቀናት ውስጥ አይደሉም

    ሊታተም የሚችል የመራጮች መመዝገቢያ ቅጽ / ሊታተም የሚችል የመራጮች ቅድመ-ምዝገባ ቅጽ

     

    በራስ-አገልግል ጣቢያ ላይ መመዝገብ፦ በራስ-አገልግል ጣቢያዎች እንግሊዝኛ ለማይናገሩ ቋንቋዎች የድምጽ መስጫ መመዝገቢያ ማዘዋወሪያዎችን ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ የዚህን ድረ-ገጽ የራስ–አገልግሎት ጣቢያ ክፍልን ይመልከቱ።

    በአካል በመቅረብ በጽሐፍት ቤት ቢሮ ቀርበው ይመዝገቡ፦ ድምጽ ለመስጠት ለመመዝገብ በአካል ወደ አከባቢዎ ወደሚገኘው የጽሕፈት ቤት ቢሮ በመሄድ መመዝገብ ይችላሉ። ምርጫ ከመደረጉ በፊት ባሉት 14 ቀናት ውስጥ በአከባቢዎ ፀሐፊ ቢሮ በአካል ቀርበዉ መመዝገብ እና የነዋሪነት ማረጋገጫ ማቅረብ አለብዎት። የነዋሪነት ማረጋገጫ ሙሉ ስምዎን እና የአሁን አድራሻዎን የሚገልጽ ህጋዊ ሰነድ ሲሆን የባንክ መግለጫ፣ ጊዜዉ ያላለፈበት የ MI የመንጃ ፍቃድ ወይም መታወቂያ፣ የኪራይ ውል ወይም የፍጆታ ሂሳብን ሊያካትት ይችላል።

    የአካባቢዎን ፀሐፊ ያግኙ

    በምርጫ ላይ ድምጽ መስጠት

    በምርጫ ላይ ድምጽ ለመስጠት የሚከተሉትን መሆን አለብዎት፡-

    • የተመዘገበ የሚቺጋን ድምጽ ሰጪ
    • ቢያንስ 18 ዓመት የሞላዉ
    • በአሁኑ ጊዜ በእስር ቤት ወይም በወህኒ ቤት ውስጥ ቅጣት ላይ ካልሆኑ
    • ከምርጫ በፊት ቢያንስ ለ 30 ቀናት የተመሳሳዩ ሚቺጋን ከተማ፣ መንደር ወይም ሰፈር ነዋሪ የሆነ

    በሚስጥር ድምጽ የመስጠት መብት አለዎት። እንደ የሚቺጋን ከተማ ድምጽ ሰጪ፣ ምክንያት ሳያቀርቡ በማንኛውም ምርጫ ለማይገኝ ሰዉ የሚቀርብ ድምጽ መስጫ መጠየቅ እና በዛ ድምጽ መስጠት ይችላሉ።

     

  • በአካል ለማይገኙ ሰዎች የድምጽ መስጫ ወረቀትን ለማግኘት ማመልከት

    በሚቺንጋን (Michigan) እያንዳንዱ ድምጽ ለመስጠት የተዘገቡ ሰዎች በአካል ለማይገኙ ሰዎች የደምጽ መስጫ ወረቀት በመጠቀም ድምጻቸውን መስጠት ይችላሉ። በአካል የማይገኝን መራጭ ድምጽ መስጫን ለመጠየቅ፣ በአካል የማይገኝን መራጭ ድምጽ መስጫ ማመልከቻን መሙላት እና ማቅረብ አለብዎት።

    በአካል የማይገኝን መራጭ ድምጽ መስጫ ማመልከቻን ለመሙላት ያሉ አማራጮች፦

    • በራስ-የመተርጎም ባህሪ ያለው አሳሽን በመጠቀም ማመልከቻውን ሞልተዉ በኦንላይን ማቅረብ። በኢንተርኔት ቀጥታ መስመር ላይ በሚከተለው ያመልክቱ Michigan.gov/Vote
    • ለከተማዎ ወይም ለመንደርዎ ፀሐፊ መደወል እና የታተመ ማመልከቻ በፖስታ እንዲላክልዎ መጠየቅ። የአከባቢዎን የጽሕፈት ቤት ቢሮ በሚከተለው ያግኙ Michigan.gov/Vote፡፡
    • በፖስታ ወይም በአካል ወደ የአካባቢዎ ወይም መንደርዎ ጸሐፊ የሚመለስ ሊታተም የሚችል የተተረጎመ ማመልከቻን ማውረድ። የተተረጎሙ ቅጾችን እዚህ ይገኛሉ ፡፡
    • የተመደበውን የአከባቢ የጽሕፈት ቤት ቢሮ በአካል ተገኝተው ይጎብኙ።

    የተጠናቀቁት ማመልከቻዎች ከምርጫው ቀን በፊት አርብ እስከ 5 p.m. በተመረጠው ጸሀፊ በፖስታ፣ በኢሜል ወይም በአካል መላክ አለባቸው።

    የእርስዎን በአካል የማይገኝን መራጭ ድምጽ ወረቀትን መሙላት እና መመለስ

    የተሞላ ማመልከቻ ካስገቡ በኋላ የድምጽ መስጫ ወረቀት ወደ አድራሻዎ ይላካል። በአከባቢዎ የተመደበልዎትን ጸሃፊ ቢሮ በሚጎበኙበት ጊዜ በአካል በመቅረብ የእርስዎን በአካል የማይገኝን መራጭ ድምጽ ወረቀት ከምርጫው ቀን በ40 ቀናት ውስጥ ሊሰጥዎት ይችላል።

    የተሞላው በአካል የማይገኝ መራጭ ድምጽ መስጫ ወረቀትን ለመመለስ ያሉ አማራጮች፡-

    • የተሞላውን የድምጽ መስጫ ወረቀት በአካል ቀርበው ለተመደበው የአካባቢዎ ፀሐፊ በእጅ መስጠት። የአከባቢዎን የጽሕፈት ቤት ቢሮ በሚከተለው ያግኙ Michigan.gov/Vote፡፡
    • የተሞላውን የድምጽ መስጫ ወረቀት በፖስታ ለተመደበው የአካባቢዎ ፀሐፊ መላክ (ከምርጫ ቀን በፊት ባሉት 2 ሳምንታት ውስጥ አይመከርም)። ድምጽ መስጫዎትን በነጻ በቀላሉ መመለስ እንዲችሉ፣ ለቴምብሮች የቅድሚያ ክፍያ ኤንቨሎፕ ተካትቷል።
    • የተመደበውን የፀሐፊዎን የመቀበያ ቦታ መጠቀም። በአካባቢዎ የሚገኘውን የጸሐፊ ቢሮ እና በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የመቀበያ ቦታ በMichigan.gov/Vote ያግኙ
    • በአካል የማይገኝን መራጭ ድምጽ ወረቀትዎን ቀደም ተብሎ ድምጽ በሚሰጥበት ቦታ ላይ ወደ ድምጽ መቀበያው ለማስገባት ይዘውት ይምጡ። የእርስዎን ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ቦታዎን በሚከተልወ ይመልከቱ Michigan.gov/Vote

    በኢንተርኔት ቀጥታ መስመር ላይ የ AV የደምጽ መስጫ ማመልከቻ 

    ሊታተም የሚችል የ AV ድምጽ መስጫ ማመልከቻ 

    የአካባቢዎን ፀሐፊ እና መቀበያ ቦታን ያግኙ 

  • በሚቺንጋን (Michigan) ቀደም ብሎ ድምጽ መስጠት

    • በሚቺንጋን (Michigan) ድምጽ ሰጪዎች የድምጽ መስጫውን ቀደም ብለው ለማስገባት እና ከምርጫው ቀን በፊት ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ቦታ ላይ በአካል ቀርበው ድምጽ ለመስጠት መብት አላቸው።
    • ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ በሁሉም ግዛት እና የፌደራል ምርጫዎች ይገኛል።
    • እንደ ሚቺንጋን (Michigan) ተመዝጋቢ ድምጽ ሰጪ፣ ቀደም ብለው ድምጽ ለመስጠት በሚመጡበት ቦታ ላይ የራስዎን አስተርጓሚ ይዘው የመመጣት መብት አልዎት። ማንኛውንም ሰው የእርስዎ አስተርጓም ሆኖ እንዲያገልግልዎት መጠየቅ ይችላሉ፤ ከሚከተሉት ግለሰቦች በስተቀር፦
      • አሠሪዎ
      • የአሠሪዎ ወኪል
      • የሠራተኛ ማህበርዎ ባለስልጣን ወይም ወኪል

    ቀድመው መምረጥ ያለባችሁ መቼ ነው

    • ቀደም ብሎ ድምጽ መስጠት ጊዜ ቢያንስ ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት ያህል የሚቆይ ሲሆን፣ ከምርጫው በፊት እሁድ ላይ ያበቃል። ቀደም ብሎ ድምጽ ለመስጠት ተጨማሪ ቀናትን ለመመደብ፣ በአጠቃላይ እስከ 28 ቀናት ያህል ማኅበረሰቡ ሊወስን ይችላል።
    • ቀደም ብለው ድምጽ የመስጫ ቦታዎች ቀደም ተብሎ ድምጽ በሚሰጥባቸው ጊዜያቶች ሁሉ በእያንዳንዱ ቀን ቢያንስ ለስምንት ሰዓታት ያህል ክፍት መሆን አለባቸው።
    • ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ለሁሉም ግዛት እና የፌደራል ምርጫዎች ሲቀርብ፣ ማህበረሰቦች ለአካባቢ ምርጫዎች ቀደም ብለው ድምጽ መስጠትን ሊመርጡ ይችላሉ። ለሰዓታት እና ቀናት ህጎች አይተገበሩም፡፡

     ቀደም ብለው መምረጥ የሚችሉት መች ነው

    • ድምጽ ሰጪዎች በአከባቢያቸው የሚገኙትን ቀደም ብሎ የድምጽ መስጫ ቦታዎችን ቀደም ብሎ ድምጽ የመጫ ወቅት በአካል የድምጽ መስጫ ወረቀቱን ለማስገባት መጎብኘት ይችላሉ። ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ቦታ መራጮች ከምርጫው ቀን ቀደም ብለው፣ ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ተብሎ የተቀመጠው ወቅት የድምጽ መስጫ ወረቀታቸውን ለማስገባት የሚችሉበት የድምጽ መስጫ ሳጥን የሚመስል ነው። ከአንድ አከባቢ፣ ከተማ፣ ወይም መንደር ከመጡ ድምጽ ሰጪዎች በላይ የሚሆኑቱ በአንድ ቦታ ላይ፣ ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ቦታዎን በመጋራት ድምጽ እንዲሰጥ ሊመደቡ ይችላሉ።
    • ድምጽ ሰጪዎች ቀደም ብለው ድምጽ እንዲሰጡበት የተመደበላቸውን ቦያዎችን ከምርጫው ቀን በፊት ቀደም ብሎ እስከ 60 ቀናት ድረስ በ Michigan.gov/Vote ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ።
  • የድምጽ መስጫ ሳጥንዎ ቦታ ላይ ድምጽ ይስጡ

    በምርጫ ቀን በተመደበው የድምጽ መስጫ ቦታዎ በአካል ድምጽ መስጠት ይችላሉ። ምርጫ ቦታዎች ለእያንዳንዱ ምርጫ ከ 7 a.m. እስከ 8 p.m. ድረስ ክፍት ናቸው። የምርጫ ቦታው በሚዘጋበት ጊዜ በ 8 p.m. ላይ ድምጽ ለመስጠት ሰልፍ ውስጥ ከሆኑ፣ አሁንም ድምጽ መስጠት የሚችሉ ሲሆን የድምጽ መስጫ ወረቀትዎን ለመውሰድ ሰልፉ ላይ እንዲቆዩ ይበረታታሉ።

    እንደ የተመዘገበ የሚቺጋን ከተማ ድምጽ ሰጪ፣ አስተርጓሚን ከእርስዎ ጋር ወደ ምርጫ ቦታው የማምጣት መብት አለዎት። በምርጫዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ሰው ካልሆነ በስተቀር፣ ማንኛውንም ሰው እንደ አስተርጓሚ እንዲያገለግልዎት መጠየቅ ይችላሉ። አስተርጓሚዎ የሚከተሉትን መሆን አይችልም፦

    1. አሠሪዎ
    2. የአሠሪዎ ወኪል
    3. የሠራተኛ ማህበርዎ ባለስልጣን ወይም ወኪል

    የድምጽ መስጫ ሳጥን ለማግኘት፣ Michigan.gov/Vote ይጎብኙ።

    ወደ Michigan.gov/Vote ይሂዱ

  • በራስ-ሰር የመተርጎም ባህሪ ያለው አሳሽ በመጠቀም፣ የመራጮች ምዝገባ ሁኔታዎን ማረጋገጥ እና የድምጽ መስጫ ናሙና በ Michigan.gov/Vote ላይ ማየት ይችላሉ።


  • የድምጽ ሰጪን ማስፈራራት እና የምርጫ መከላከያ ነጻ መስመር

    ድምጽ ሰጪዎች ያለምንም ማስፈራራት ድምጻቸውን ለመስጠት መብት አላቸው። የድምጽ ሰጪዎችን ድምጽ የመስጠት መብት ውስጥ ጣልቃ መግባት ሕገወጥ ነው። የድምጽ ሰጪን ማስፈራሪያ በተመለከተ ሪፖርት ለማድረግ የምርጫ መከላከያ ነጻ መስመርን ይጠቀሙ።

    የድምጽ ሰጪን ማስፈራራት የሚያጠቃልላቸው፣ ነገር ግን በዚህ ብቻ የማይወሰን፡

    • የምርጫው ሠራተኞች ያልሆኑ ወይም የምርጫዎ ባለሥልጣናት ያልሆኑ ድምጽ ሰጪዎችን የግል ሰነዶችን የሚጠይቁ ግለሰቦች
    • ያለ እነርሱ ስምምነት የድምጽ ሰጪዎችን ፎቶ የሚያነሱ ወይም ቪዲዮ የሚቀርጹ
    • ወደ ደምጽ መስጫ ሳጥን መግቢያ፣ የጽሕፈት ቤት ቢሮ፣ ወይም የቀሪ የድምጽ መስጫ ወረቀት መመለሻ ሳጥንን የሚዘጉ
    • ደምጽ ሰጪዎችን የሚጠይቁ ወይም የሚያንቋሽሹ
    • ሐሰት የሆነ ወይም የሚያሳስተውን የምርጫመረጃን ማሰራጨት

    የድምጽ መስጫ ወረቀትዎን ሲያስገቡ ወይም ከምርጫው በፊት እነዚህ ነገሮች ቢያጋጥምዎት፣ ወይም የድምጽ መስጫ ሂደቱን በተመለከተ ጥያቄዎችን ካልዎት፣ የምርጫ መከላከያ ነጻ መስመርን በመጠቀም እገዛ ለማግኘት ያግኙን፦

    • ለእንግሊዝኛ፦ 866-OUR-VOTE (866-687-8683)
    • ለስፓንሽ፦ 888-VE-Y-VOTA (888-839-8682)
    • ለዓረብኛ፦ 844-YALLA-US (844-925-5287)
    • ቤንጋሊ፣ ካንቶኒዝ ሂንዲ፣ ኮሪያኛ፣ ማንዳሪን፣ ታጋሎግ፣ ኡርዱ እና ቬትናምኛ፦ 888-API-VOTE (888-274-8683)

    የቋንቋ አገልግሎት ማግኘት

    የሚቺንጋን (Michigan) ነዋሪዎች እንግሊዝኛ የአፍ መፍቻው ያልሆነን ተርጓሚ ወደ ጽሕፈት ቤት ቢሮ፣ ቀደም ተብሎ ድምጽ ለሚሰጥበት ቦታ ላይ ወይም ወደ ድምጽ መስጫ ሳጥን ድምጽ ለመስጠት ድጋፍ ለማግኘት ይዘው መምጣት መብት አላቸው። አስተርጓሚዎ በምርጫዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር አይችልም፤ አሠሪዎ፣ የአሠሪዎ ወኪል ወይም የሠራተኛ ማህበርዎ ባለስልጣን ወይም ወኪል አስተርጓሚዎ ሊሆን አይችልም።

    ምንም ዓይነት የሚታወቁበት ፎቶ አያስፈልግም

    የፎቶ መለያዎ ከእርስዎ ጋር ከሌለ፣ አሁንም ድምጽ መስጠት ይችላሉ። በድምጽ መስጫ ቦታዎች የፎቶ መታወቂያ የሌለበት የመራጭነት ማረጋገጫ ማጠናቀቅ ይጠበቅብዎታል።

    ምክንያት ሳይኖራቸው የቀሩ ድምጽ ሰጪዎች

    በሚቺንጋን (Michigan) ውስጥ ድምጽ ለመስጠት እያንዳንዱ ተመዝጋቢ የ የቀሪ ድምጽ መስጫን በመጠቀም ከቤት ድምጽ ለመስጠት፣ ቀደም ብሎ ድምጽ መስጠት፣ ወይም በፖስታ ድምጽ ለመስጠት መብት አላቸው። የበለጠ ለመማር፡፡

    በተመሳሳይ ቀን ድምጽ ለመስጠት መመዝገብ

    ብቁ የሆኑ የሚቺጋን ከተማ ነዋሪዎች በምርጫ ቀን ድምጽ ለመስጠት የተመደበውን የአካባቢ ፀሐፊ ቢሮን በመጎብኘት እና የነዋሪነት ማረጋገጫን በማቅረብ መመዝገብ ይችላሉ። የነዋሪነት ማረጋገጫ የእርስዎን የአሁኑን ስም እና አድራሻ የያዘ ሕጋዊ ሰነዶች ማለት ሲሆን፣ የሚያጠቃልለውም (ነገር ግን በዚህ ብቻ የማይወሰን) የመንጃ ፈቃድ ወይም የግዛቱ መታወቂያ፣ የፍጆታ ደረሰኞች፣ የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ መግለጫ፣ ወይም የክፍያ ቼክን ያካትታል፡፡ የበለጠ በዚህ ላይ ይወቁ Michigan.gov/VoterRegistration፡፡

    ተመላሽ ዜጎች

    በሚቺንጋን (Michigan) ውስጥ፣ ተመላሽ ዜጎች፣ ወይም ያለፈው ጊዜ ጥፋት የነበራቸው ግለሰቦች፣ ምንም እንኳን በይቅርታ ወይም በክልከላ ላይ ያሉት እንኳን ቢሆኑ ለመመዝገብ ብቁ ናቸው። ከምርመራ በፊት ወይም ፍርዳቸውን እየጠበቁ ያሉ በእስር ላይ የሚገኝ ሰው ድምጽ ለመስጠት ለመመዝገብ እና ድምጽ ለመስጠት ቀሩ ለሆኑ ድምጽ መስጫ ወረቀትን በተመለከተ ለመመዝገብ ብቁ ናቸው። በእስር ቤት ወይም በወህኒ ቤት ውስጥ ለአንድ ሰው መመዝገብ እና ድምጽ መስጠት የተከለከለው በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ለታሰሩ ሰዎች ብቻ ነው። የበለጠ በዚህ ላይ ይወቁ Michigan.gov/VoterRegistration፡፡

    የድምጽ ሰጪ ተደራሽነት

    የሚቺጋን (Michigan) ድምጽ ሰጪዎች ተደራሽ የሆኑ የምርጫ ቦታዎችን የማግኘት እና የድምጽ አሰጣጥ እርዳታ ለማግኘት የመራጮች እርዳታ ተርሚናሎችን (Voter Assist Terminals፣ VATs) የመጠቀም መብት አላቸው። VAT ቶች የመስማት፣ የዕይታ፣ አካላዊ እክሎች እና ለሌሎች የአካል ጉዳቶች ላለባቸው ሰዎች፣ የምርጫ ካርዳቸው ላይ ምልክት ለማድረግ የሚረዱ የልዩ ሁኔታዎች መሳሪያዎች ናቸው። መራጮች VAT ን በመጠቀም በነፃነት እና በግል የመምረጥ መብት አላቸው እና በቦታው ላይ የምርጫ ተቆጣጣሪዎች (የድምጽ መስጫ ቦታ ሰራተኞች) ሲጠየቁ ለመርዳት ወይም መመሪያ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።

  • የሚከተሉት ማኅበረሰቦች በተወሰኑ ቋንቋዎች የተተረጎሙ የምርጫ ስነዶችን ያቀርባሉ።

    • የ(ዴኣብሪብ (Dearborn) ከተማ፦ ዓረብኛ
    • የሃምትራምክ ከተማ፦ አረብኛ እና ቤንጋሊ
    • የ ፌንቪሌ (Fennville) ከተማ፦ ስፓንሽ
    • የክላይድ ከተማ፦ ስፓኒሽ

    የኮቨርት ከተማ፦ ስፓኒሽ

    እንግሊዘኛ ማንበብ ወይም መጻፍ የማይችሉ ከሆነ እና በቋንቋዎ የድምጽ መስጫ ወረቀት ከሌለ ከፈለጉት ሰው እርዳታ የማግኘት መብት አለዎት። ነገር ግን ግለሰቡ የሚከተለውን መሆን አይችልም፦

    • አሠሪዎ
    • የአሠሪዎ ወኪል
    • የሠራተኛ ማህበርዎ ባለስልጣን ወይም ወኪል

    iii) እንደ የተመዘገበ የሚቺጋን ከተማ ድምጽ ሰጪ፣ አስተርጓሚን ከእርስዎ ጋር ወደ ምርጫ ቦታው የማምጣት መብት አለዎት። "የድምጽ መስጫ መብቶችን" ቀደም ብለው በዚህ ገጽ ላይ ለበለጠ መረጃ ይመልከቱ።

  • በምርጫ ቀን ወይም ከዚያ በፊት ድምጽዎን ለመስጠት ምንም አይነት ችግር ካጋጠመዎት፣ እርዳታ ለማግኘት የምርጫ ጥበቃ የስልክ መስመርን (Election Protection Hotline) ያነጋግሩ፦

    • ለእንግሊዝኛ፦ 866-OUR-VOTE (866-687-8683)
    • ለስፓንሽ፦ 888-VE-Y-VOTA (888-839-8682)
    • ለዓረብኛ፦ 844-YALLA-US (844-925-5287)
    • ቤንጋሊ፣ ካንቶኒዝ ሂንዲ፣ ኮሪያኛ፣ ማንዳሪን፣ ታጋሎግ፣ ኡርዱ እና ቬትናምኛ፦ 888-API-VOTE (888-274-8683)
     

ቅጾች እና ህትመቶች

የቅጾች እና የህትመቶች ምናሌን በመጠቀም የተተረጎሙ የምርጫ መርጃዎችን እና ቁሳቁሶችን ይፈልጉ። በመረጡት ቋንቋ የተተረጎሙ ሰነዶችን ለማየት የቋንቋ ማጣሪያውን ይጠቀሙ።

የተተረጎመ ሰነድ መጠየቅ

የተተረጎመውን ሰነድ ለመጠየቅ፣ እባክዎን በዚህ ላይ ኢሜይል ያድርጉ MDOS-Access@Michigan.gov። እባክዎን የሚከተለውን መረጃ በኢሜይል መጠይቅዎ ውስጥ ያካትቱ፦

  • የሰነዱ ስም
  • ለትርጉም የተጠየቀው ቋንቋ